ዲቫይን ዋችኩዋ ከቡናማዎቹ ጋር ይቆያል

ዲቫይን ዋችኩዋ ከቡናማዎቹ ጋር ይቆያል

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል

በዛሬው ዕለት የነባሮቹ አማኑኤል አድማሱ ፣ ይታገሱ ታሪኩ ፣ ኤርምያስ ሹምበዛ እና ረጂብ ሚፍታሕን ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም የተስማሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች አሁን ደግሞ የናይጄርያዊው አማካይ ዲቫይን ዋችኩዋ ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።

ላለፉት ሁለት ዓመታት በቡናማዎቹ ቤት ቆይታ የነበረው አማካዩ ቤንደል ኢንሹራንስን ለቆ ወደ ቡናማዎቹ ቤት ባመራበት ከስኬታማው የመጀመሪያ ዓመቱ በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት መጠነኛ መቀዛቀዝ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም የኋላ ኋላ ወደ ቋሚነት ተመልሶ በጥሩ ብቃት ዓመቱን ማገባደዱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት በቡድኑ ለመቆየት ተስማምቷል።