ነብሮቹ የመጀመርያ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል

ነብሮቹ የመጀመርያ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ስድስት ስኬታማ ወራት ያሳለፈው አጥቂ ወደ ሀድያ ሆሳዕና ለማምራት ተስማምቷል

አሰልጣኝ ሳምሶም አየለን ዋና አሰልጣም አድርገው የሾሙት ሀድያ ሆሳዕናዎች ወደ ክረምቱ የዝውውር መስኮት በመግባት የመጀመርያ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል። ነብሮቹን የተቀላቀለው ተጫዋችም አጥቂው ቢኒያም ጌታቸው ሆኗል።

በሀምበሪቾ ፣ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በድሬደዋ ከተማ፣ በፋሲል ከተማ የተስጫወተው አጥቂው በውድድር ዓመቱ አጋማሽ ኢትዮጵያ ቡናን በመቀላቀል ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር ጥሩ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ አሁን ደግሞ በሁለት ዓመት ውል ለነብሮቹ ለመጫወት ተስማምቷል።