በ2026 በሴካፋ ዞን የሚካሄዱ ስድስት ውድድሮችን የሚያስተናግዱ ሀገራት ይፋ ሆነዋል

የሴካፋ ጊዜያዊ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ዣን ሴኒንዴ በዛሬው ዕለት በ2026 በዞኑ የሚከናወኑትን ውድድሮች ለማስተናገድ የተመረጡ አባል ሀገራት ይፋ አደረጉ። በዚህ መሰረት ታንዛኒያ የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ቻምፒዮና እና የቶታል ኢነርጂስ የካፍ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ቻምፒዮና ማጣሪያ ለማስተናገድ ስትመረጥ ሩዋንዳ ደግሞ የሴካፋ ክለቦች ካጋሜ ካፕ፣ የካፍ የአፍሪካ ትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ቻምፒዮና የሴካፋ ዞን ማጣሪያ፤ የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ እና የቶታል ኢነርጂስ የካፍ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድሮችን ታስተናግዳለች።

