ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾች በክለቡ ለማቆየት ተስማምቷል

አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና ውላቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ቡድናቸውን ለማጠናከር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች የሁለት ተጫዋቾቻቸውን ውል ማራዘማቸው ታውቋል።።
ውሉን ያራዘመው የመስመር ተከላካዮ ረጀብ ሚፍታሕ በኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ በከፍተኛ ሊግ ቤንች ማጂ ቡናና በባህርዳር ከተማ ያደረጋቸውን ቆይታዎች አጠናቆ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ አሳዳጊው ቡደን ደግም በመምጣት ሲያገለግል መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት በቡድኑ ለመቆየት ተስማማቷል።
ሌላው አማካይ ኤርሚየስ ሹምበዛ ከወልቂጤ ከተማ መነሻውን አድርጎ ያለፉትን አራት ዓመት ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን በጥሩ ብቃት የዘለቀ ሲሆን አሁን ደግሞ በቡድኑ ለመቆየት መስማማቱን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

