አማኑኤል አድማሱ ውሉን ለማራዘም ተስማማ

አማኑኤል አድማሱ ውሉን ለማራዘም ተስማማ

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች የነባር ተጫዋቾች ውል ወደ ማራዘሙ ገብተዋል

ቀደም ብለው አቡበከር ኑራ ፣ በረከት ወልደ ዩሐንስ ፣ አብዱልሰላም የሱፍ እና ሀብታሙ ተከስተን ለማስፈረም የተስማሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች የፊት መስመር ተጫዋቹ አማኑኤል አድማሱን ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል። ከሐረር ሲቲ ታዳጊ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን አምርቶ በቡድኑ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ቆይታ ካደረገ በኋላ ላለፉት አራት ዓመታት ዋናው ቡድኑን ያገለገለው አማኑኤል አሁን ደግሞ በቡናማዎቹ ቤት ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል።