በኢትዮጵያ መድን ቆይታ የነበረው አማካይ መዳረሻው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆኗል

በወላይታ ድቻ ተስፋ ቡድን የተገኘው እና ያለፉትን ዓመታት በኢትዮጵያ መድን ቆይታ ያደረገው አማካዩ ብሩክ በላቸው ወደ ፈረሰኞቹ ለማቅናት ከስምምነት ደርሷል። ከጨዋታ ጨዋታ እራሱን እያሻሻለ የመጣውና የሚጫወትበት ስፍራ ከመስመር አጥቂነት ወደ አማካይነት የቀየረው ብሩክ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሃያ ስምንት ጨዋታዎች ተሰልፎ 1787 ደቂቃዎች ቡድኑን በማገልገል ሁለት ጎሎች ማስቆጠሩ ይታወሳል።
ፈረሰኞቹ አሁን ለሁለት ዓመታት ቡድኑን ለማገልገል ከተማማው ብሩክ በላቸው በተጨማሪ ብሩክ እንዳለ ፣ ተመስገን ብርሃኑ እና አጥቂውን ቢላል ገመዳን ለማስፈረም ተስማምተው የፀጋ ከድር እና የብሩክ ታረቀኝን ውል ማራዘማቸው ይታወሳል።

