በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ መድረክ የሚሳተፉ የሀገራችን ክለቦች ተጋጣሚዎቻቸውን የሚያውቁበት ቀን ታውቋል

በ2026/27 የካፍ ቻምፕዮንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፉት የሲቢኢ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ሲዳማ ቡናና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው ወልዋሎ በቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር የሚገጥሟቸውን ቡድኖች በቅርቡ ይታወቃሉ።
ታማኙ የሞሮኮ ሚድያ አል ቦቶላ ከአንድ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የክለቦች ውድድር ኮሚቴ አባል ከሆነ ግለሰብ አገኘሁት ብሎ ባወጣው መረጃ መሰረት ኮሚቴው የሁለቱም አህጉራዊ ውድድሮች የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ሐሙስ ሐምሌ 30 በግብፅ መዲና ካይሮ እንዲካሄድ መወሰኑ ታውቋል። በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉራዊ መድረክ የሚሳተፉት ሲዳማ ቡናና ወልዋሎም በዕለቱ ተጋጣሚዎቻቸው የሚያውቁ ይሆናል።

