ድሬዳዋ ላይ የፊታችን ማክሰኞ የሚደረገው የኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ጨዋታ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኝ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ተደልድሎ የመጀመሪያ ጨዋታውን ሞሮኮ ላይ አድርጎ የሦስት ለምንም ድል የተቀዳጀ ሲሆን የመልሱን ጨዋታ ደግሞ በድሬዳዋ ስታዲየም የፊታችን ማክሰኞ ያከናውናል።
ባሳለፍነው ዓርብ በኤል-አብዲ ስታዲየም የተደረገውን ጨዋታ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዩ ቱብ ገፁ በቀጥታ በማስተላለፍ ጨዋታውን ተደራሽ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የማክሰኞ ጨዋታ ደግሞ በድሬ ቲቪ በቀጥታ ለአድማጭ ተመልካቾች እንደሚተላለፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

