የሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ዋና አሰልጣኝ  ምን አሉ?

የሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ዋና አሰልጣኝ ምን አሉ?

👉 “ኢትዮጵያን ሁሌም በልቤ አኖራታለሁ”

👉 “በትላልቅ የአውሮፓ ሊጎች የመጫወት አቅም ያላቸው ተጫዋቾች አሏቸው”

👉 ያለብን የልምድ ማነስ የፈለግነውን እንዳናደርግ ገድቦናል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ከሆነው ሪካርዶ ሞንሳንቶ ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ እንደሚከተለው አቅርበናል።

“በኢትዮጵያ የነበረኝ ቆይታ እጅግ ደስ የሚል ሲሆን ኢትዮጵያ ተወዳጅ የሆኑ ህዝቦችም አሏት። ኢትዮጵያን ሁሌም በልቤ አኖራታለሁ።”

“ኢትዮጵያ አጅግ ጠንካራና ጥሩ ተጫዋቾች አሏቸው በተለይም የፊት መስመር ላይ የነበሩት መስፍን ታፈሰ ፣ አቤል ያለውና ቸርነት ጉግሳ ሳላደንቅ ማለፍ አልችልም ችሎታቸው በፖርቹጋልና በሌሎች ትላልቅ የአውሮፓ ሊጎች ጋር መጫወት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው ተመልክቻለሁ።”

“ሞሮኮና ኢትዮጵያ ባደረግናቸው በሁለቱም ዙሮች ቡድናችን ጥሩ መንቀሳቀስ የቻለ ቢሆንም ያለብን የልምድ ማነስ እና የግብ ማስቆጠር ችግር የፈለግነውን እንዳናደርግ ገድቦናል።”