👉 “ባለን አጭር ጊዜ ሳይኮሎጂካሊ በደንብ ለመዘጋጀት ሞክረናል”
👉 “ትውልደ ኢትዮጵያኖች ሀገራቸውን ቢያገለግሉ ለኛ እጅግ ትልቅ ጥቅም ነው የሚኖረው”
👉 “በሜዳችንና በደጋፊዎቻችን ፊት መጫወታችን ለእኛ እጅግ ትልቅ ጉልበት ፈጥሮልናል”
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ አቻውን 1-0 ካሸነፈበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሰጡትን አስተያየት እንደሚከተለው አቅርበናል።

“ባለን አጭር ጊዜ ሳይኮሎጂካሊ በደንብ ለመዘጋጀት ሞክረናል ነገር ግን አሁንም ሊስተካከሉ የሚገቡ ብዙ ችግሮች እንዳሉ ተመልክተናል።”
“ትውልደ ኢትዮጵያኖች ባላቸው ችሎታ ተመዝነው ወደዚህ መጠው ሀገራቸውን ቢያገለግሉ ለኛ እጅግ ትልቅ ጥቅም ነው የሚኖረው። ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ማድረግ አለባቸው።”
“በሜዳችንና በደጋፊዎቻችን ፊት መጫወታችን ለእኛ እጅግ ትልቅ ጉልበት ፈጥሮልናል። ወደፊትም በሀገራችን የምንጫወትበት ሁኔታዎች ሊመቻች ይገባል።”
“በቡድናችን ላይ የነበረው ጥሩ የሆነ የቡድን ስሜት መኖሩና ስነልቦና ላይ አትኩረን መስራታችን አሁን ለመጣው ስኬት ቁልፍ ሚና ተጫውቶልናል።”

