አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ከሐይቆቹ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት ደርሰዋል

አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ከሐይቆቹ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት ደርሰዋል

አሰልጣኝ ተመስገን ዳን በሀዋሳ ከተማ ለተጨማሪ ዓመት እንዲቆዩ የክለቡ ቦርድ ወስኗል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሀዋሳ ከተማ በዋና አሰልጣኝነት የተረከቡት አሰልጣኝ ተመስገን ዳና የነበራቸው የአንድ ዓመት ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ ትናንት ማታ ስብሰባ የተቀመጠው የክለቡ ቦርድ አሰልጣኙ ለተጨማሪ ዓመታት ቡድኑ እያሰለጠኑ እንዲቆዮ መወሰኑን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

አሰልጣኝ ተመስገን ከዚህ ቀድም በሀዋሳ ወጣት ቡድን በመሰልጠን ብዙ ተስፈኞችን በማፍራት ሲታወቁ በመቀጠል በደቡብ ፖሊስ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ በኢትዮጵያ ቡና ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ዋና አሰልጣኝ እና የዋናው ብሔራዊ ቡድን ምክትል በመሆን መስራታቸው ይታወቃል።