የሙታክብዋ ጆኤል ማረፍያ ታውቋል

የሙታክብዋ ጆኤል ማረፍያ ታውቋል

ከወልዋሎ ጋር ስኬታማ ጊዜ ማሳለፍ የቻለው ግብ ጠባቂ አዲስ ክለብ አግኝቷል።

በ2018 የውድድር ዓመት ስኬታማ ጊዜ ካሳለፉ ግብ ጠባቂዎች አንዱ የሆነው እና ከወልዋሎ ጋር የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ የነበረው ዩጋንዳዊው ጆኤል ሙታክብዋ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ኪታራን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል። ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከሀያ ዘጠኝ ጨዋታዎች ውስጥ በአስራ አራቱ መረቡን ሳያስደፍር በመውጣት ስኬታማ ጊዜ ካሳለፈበት ቡል ጋር የነበረውን ውል አጠናቆ ወደ ወልዋሎ በማምራት ከቢጫዎቹ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው ግብ ጠባቂው አሁን ደግሞ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ለኪታራ ለመጫወት ተስማምቷል።

በ2025 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ላይ ሀገሩ ዩጋንዳን ወክሎም በስድስት ጨዋታዎች በቋሚነት የተሰለፈው ጆኤል ከዚህ ቀደም በሀገሩ ክለቦች ክየቱሜ፣ ኤክስፕረስ እንዲሁም ኢንቴቤ እና ቡል መጫወቱ የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአንድ ዓመት የኢትዮጵያ ቆይታ በኋላ ዳግም ወደ ሀገሩ ተመልሷል።