ቀደም ብለው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ለማስቀጠል የተስማሙት ወላይታ ድቻ ወደ ዝውውሩ ገብተዋል

ቀደም ብለው የዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ውል ለማራዘም የተስማሙት ወላይታ ድቻዎች አሁን ደግሞ ቡድናቸውን ወደ ማጠናከር ተሸጋግረው የአንድ ነባር ተጫዋች ውል ለማራዘም እንዲሁም አንድ ተጫዋች ለማስፈረም ለስምምነት ደርሰዋል።
ቀዳሚው ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው የግራ መስመር ተከላካዩ ኤፍሬም ታምራትን ነው ፤ በከምባታ ዱራሜ እግርኳስን መጫወት የጀመረው ኤፍሬም ከዚህ ቀደም በቤንች ማጂ ቡና ፣ ኢትዮጰያ ንግድ ባንክ እና አርባምንጭ ከተማ መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ በሁለት ዓመት ውል የጦና ንቦቹን ለመቀላቀል ተስማምቷል። በቡድኑ ለመቆየት የተስማማው ደግሞ ተከላካዩ ውብሸት ክፍሌ ነው፤ ከወላይታ ድቻ ተስፋ ቡድን የተገኘው እና ቀደም ብሎ በሶዶ ከተማ ፣ ቦዲቲ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ባለፉት ዓመታት ዳግም ወደ እናት ክለቡ ተመልሶ ቡድኑን ማገልገሉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በወላይታ ድቻ ለመቆየት ተስማምቷል።

