የግብ ዘቡ አቡበከር ኑራ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተቃርቧል

የግብ ዘቡ አቡበከር ኑራ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተቃርቧል

ሁለት ጊዜ የሊጉ ኮከብ ግብ ጠባቂ የተባለው አቡበከር ኑራ መዳረሻው የት እንደሆነ ታውቋል

ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያለፉትን ዓመታት ስኬታማ ቆይታ ያደረገው የግብ ዘቡ አቡበከር ኑራ የውል ዘመኑ መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቢቆይም አሁን መዳረሻው ኢትዮጵያ ቡና ለመሆን ከጫፍ መድረሱን ሰምተናል።

በመቱ የጀመረው የግብ ጠባቂነት ሕይወቱ ወደ ጅማ አባ ጅፋር ከመጣ በኋላ ራሱን በሊጉ ማስተዋወቅ የቻለው አቡበከር በመቀጠል በባህር ዳር ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላ ያለፉትን አራት ዓመታት ከኢትዮጵያ መድን ጋር ስኬታማ ዓመታትን ያሳለፈ ሲሆን ሁለት ጊዜ የሊጉ ኮከብ ግብ ጠባቂ እና አንድ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወቃል።

የብሔራዊ ቡድኑ ቁጥር አንድ ግብጠባቂ የሆነው አቡበከር አብረውት ከሰሩት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ በመቀጠል ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለ የመጀመርያው ፈራሚ ለመሆን ተቃርቧል።