በነገሌ አርሲ ቆይታ የነበረው በረከት ወልዴ ወደ ጦና ንቦቹ ተመልሷል።
ቀደም ሲል የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እንዲሁም የአማካዮቹ ቴዎድሮስ ታፈሰ እና የመሳይ ኒኮልን ውል ያራዘሙት ወላይታ ድቻዎች አሁን ደግሞ የቀድሞ ተጫዋቻቸው አማካዩ በረከት ወልዴን ማስፈረማቸው ተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጧል። የእግርኳስ ህይወቱን በወላይታ ድቻ ከታዳጊ እስከ ዋና ቡድን ድረስ ከተጫወተ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ደግሞ በነገሌ አርሲ ያሳለፈው አማካዩ አሁን ደግሞ ዳግም ወደ አሳዳጊ ክለቡ ተመልሶ ለመጫወት መስማማቱን አውቀናል።

