ግብ ጠባቂው ወደ ሀገሩ ተመልሷል

ግብ ጠባቂው ወደ ሀገሩ ተመልሷል

የውድድር ዓመቱን በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፈው ግብ ጠባቂ ወደ ሀገሩ ተመልሷል።

ፋሩክ ሺካሎ ከሀገሩ ክለብ ኬሲቢ ናይሮቢ ጋር ከተለያየ በኋላ የተጠናቀቀው የውድድር ዓመትን በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፈ ሲሆን በ32 የሊግ ጨዋታዎች ላይ የፈረሰኞቹን ግብ ጠብቋል። ተጫዋቹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት በኢንስታግራም ገጹ የምስጋና መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ናይሮቢ ዩናይትድን በይፋ ተቀላቅሏል።

ሺካሎ ለኬንያ ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም ባንዳሪ፣ ፖስታ ሬንጀርስ፣ ካካሜጋ ሆምቦይ እና ያንግ አፍሪካ ክለቦች ተጫውቷል።