የቢጫዎቹ የዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ፈራሚ ታውቋል

የቢጫዎቹ የዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ፈራሚ ታውቋል

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊዎቹ የመስመር አጥቂውን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊዎቹ ወልዋሎዎች ከቀናት በፊት የዋና አሰልጣኙ ግርማ ታደሰን ውል ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ሲታወቅ በትናንትናው ዕለት ደግሞ የመሃል ተከላካዩ ነፃነት ገብረመድኅን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ ከቀናት ድርድር በኋላ ባለፉት ዓመታት በሀዲያ ሆሳዕና ቆይታ የነበረው የፊት መስመር ተጫዋቹ ኢዮብ ዓለማየሁን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። በወላይታ ድቻ ታዳጊ ቡድን ፍሬ የሆነው ኢዮብ በ2008 ወደ ዋናው ቡድን አድጎ አሳዳጊ ክለቡን ካገለገለ በኋላ በጅማ አባጅፋር ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና መጫወቱ የሚታወስ ነው።