አሕመድ ረሺድ ወደ ሌላው የሊጉ ክለብ አምርቷል

በዝውውር መስኮቱ የነፃነት ገ/መድህን ፣ ሰመረ ሀፍታይ እና የስምኦን ማሩን ውል ለማራዘም ተስማምተው እዮብ አለማዮህ ፣ በረከት ሳሙኤል ፣ ካርሎስ ዳምጠው እና ማማዱ ሴክ ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ሁለገቡን ተጫዋች ለማስፈረም ተስማምተዋል። ክለቡን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ተጫዋች ደግሞ በመሀል ተከላካይነት እና በመስመር ተከላካይነት የሚጫወተው አሕመድ ረሺድ ሲሆን ለቀናት ካደረገው ድርድር በኋላም ከደቂቃዎች በፊት ክለቡን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቡና ፣ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ያገለገለው ተጫዋቹ ቢጫዎቹን ለመቀላቀል የተስማማ አምስተኛ ተጫዋች ሆኗል።

