ሸገር ከተማ ወደ ዝውውሩ ገብቷል

ሸገር ከተማ ወደ ዝውውሩ ገብቷል

ሸገር ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋች ውል አራዝሟል

በጊዝያዊ አሰልጣኝነት ቡድኑን ሲመሩ የቆዩት አሰልጣኝ እያሱ መርሃፅድቅን ዋና አልጣኝ አድርጎ የሾመው ሸገር ከተማ ወደ ዝውውሩ በመግባት የገዛህኝ ደሳለኝ ውል ሲያራዝም የመለሰ ሚሻሞ፣ ፉአድ ፈረጃ እና ብሩክ ባይሳን ወደ ክለቡ ለመቀላቀል ተስማምቷል

የእግር ኳስ ሂወቱ በኢትዮጵያ ቡና የጀመረው ተከላካዩ ገዛኸኝ በሻሸመኔ ፣ ለገጣፎ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በተጠናቀው የውድደር ዓመት በሸገር ከተማ ያሳለፈውን ጥሩ ጊዜን መሠረት በማድረግ ለሁለት ዓመት የሚያቆየውን ውል አራዝሟል።

የክለቡ የመጀመርያ ፈራሚ የሆነው መለሰ ሚሻሞ ደግሞ በቡራዮ ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ትውልድ ከተማ ክለቡ ሀድያ ሆሳዕና በመመለስ ያለፉትን ዓመታት በነብሮቹ ሲጨወት ቆይቶ አሁን መዳረሻው ሸገር ከተማ ሆኗል።

ሌላኛው ክለቡን የተቀላቀለው ተጫዋች ፉአድ ፈረጃ ነው፤ በአዳማ ከተማ፣ በባህር ዳር ከተማ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ ያደረገው ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ማረፊያው ሸገር ከተማ እንዲሆን ተስማምቷል። ሦስተኛው ቡድኑ የተቀላቀለው ፈራሚ ተከላካዩ ብሩክ ባይሳ በአርባምንጭ ከተማ የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ማረፊያውን ሸገር ከተማ ለማድረግ ተስማምቷል።