በርከት ያሉ የዝውውር ሂደቶችን እየፈፀሙ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ተከላካይ ለማስፈረም ተቃርበዋል

ለ2019 የውድድር ዘመን ራሳቸውን አጠናክረው ለመቅረብ በዝውውሩ ሂደት ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ፈረሰኞቹ ወጣቱን የመሐል ተከላካይ ቢኒያም በቀለን ለማስፈረም መቃረባቸው ታውቋል።
ቁመታሙ ተከላካይ የእግርኳስ መነሻውን በመቻል ታዳጊ ቡድን አድርጎ በኋላም በኢትዮ ኤሌክትሪክ ተስፋ ቡደን ባሳየው ዕድገት ወደ ዋናው ቡድን ካደገ ሁለት ዓመት የሆነው ቢኒያም ዘንድሮ ለቡድኑ በሠላሳ ሦስት ጨዋታዎች ላይ 3889 ደቂቃዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ ጠንካራ ተከላካይነቱን ያሳየ ሲሆን አሁን መዳረሻውን ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ በማድረግ ለሁለት ዓመት መፈረሙ ታውቋል።

