ከአርባምንጭ ከተማ ጋር በግሉ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው ግብ ጠባቂው መዳረሻው የፈረሰኞቹ ቤት ለመሆን ተቃርቧል።

ፅዮን መርዕድ በአርባምንጭ ከተማ የግብ ጠባቂነት ሕይወቱን መነሻ አድርጎ በመቀጠል በወላይታ ድቻ፣ በሀዋሳ ከተማ፣ በባህር ዳር ከተማ በድጋሚ ወደ ቀድሞ ክለቡ በመመለስ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአርባምንጭ ሲያገለግል ቆይቷል።።
ዘንድሮ የውል ጊዜው ያበቃው ፅዮን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለመጫወት መስማማቱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

