በአሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ የሚመሩት ጋሞ ጨንቻዎች የአምስት ተጫዋቾች ውል አራዘሙ
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 2018 ውድድር ዓመት በምድብ “ሀ” ተደልድሎ ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቅ ወደ በ2019 የውድድር ዓመት በሲቢኢ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ ለ2019 የውድድር ዓመት ቡድኑን ለማጠናከር ወደ እንቅስቃሴው ገብቷል። በዛሬው ዕለት ወደ እንቅስቃሴ የገባው ጋሞ ጨንቻ ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ትልቅ አስተዋፅዖ ያደረጉትን የዘካርያስ ተክሌ ፣ አኮ ቦቃ ፣ ዘካርያስ ጆብሮ ፣ ሳሙኤል ጃጊሶና የትም ጌታ ታደሰ ውል ለተጨማሪ ዓመታት በማራዘም ወደ ዝውውሩ ገብቷል።

