ሀምራዊዎቹ ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ ገብተዋል

ሀምራዊዎቹ ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ ገብተዋል

የ2016 ቻምፒዮኖቹ ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የአራት ነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ መግባት ችለዋል።

በአሰልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ የሚመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የአራት ነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ መግባታቸው ታውቋል።

ከታዳጊ ቡድን ያደገው እና ዘንድሮ የመሰለፍ ዕድል ያገኘው ተስፈኛው ግብ ጠባቂ አማኑኤል ደስታ፣ ከተስፋ ቡድኑ ያደገው እና በዚህ በተጠናቀቀው ዓመት ለመጀመርያ ጊዜ መጫወት የቻለው ተስፈኛው የቀኝ መስመር ተከላካይ አቤኔዜር ተክሉ፣ ንግድ ባንክ ወደ ሊጉ ሲያድግ ቁልፍ ሚና የነበረው እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከቡድኑ ጋር የቆየው ዘንድሮ ባመዛኙ ጨዋታዎች ላይ መሳተፍ የቻለው አማካዩ ብሩክ ብፁዕአምላክ እና ባለ ተሰዕጦው ዓምና ከተስፋ ቡድን በማደግ ተስፋ ሰጪ ዕድገት እያሳየ የሚገኘው አማካይ ዮሐንስ ኪዳኔ በቡደኑ ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ውል ማራዘሙ ተጫዋቾች ናቸው።

የ2016 የሊጉ አሸናፊ ሆነው ያጠናቀቁት ንግድ ባንኮች በቀጣዮቹ ቀናት ቡድናቸውን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ በስፋት እንደሚገቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።