በአሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ የሚመሩት ጋሞ ጨንቻዎች የአምስት ተጫዋቾች ውል አራዘሙ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ “ሀ” ተደልድሎ ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቅ ወደ በ2019 የውድድር ዓመት በሲቢኢ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ ለ2019 የውድድር ዓመት ቡድኑን ለማጠናከር ወደ እንቅስቃሴው ገብቷል። በዛሬው ዕለት ወደ እንቅስቃሴ የገባው ቡድኑ የዘካርያስ ተክሌ ፣ አኮ ቦቃ ፣ ዘካርያስ ጆብሮ ፣ ሳሙኤል ጃጊሶና የትም ጌታ ታደሰ ውል ለተጨማሪ ዓመታት በማራዘም ወደ ዝውውሩ ገብቷል።

