የግራ መስመር ተከላካዩ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

የግራ መስመር ተከላካዩ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ደስታ ዮሐንስ አዲስ ክለብ አግኝቷል።

የአሰልጣኝ ተመስገን ዳና እንዲሁም የብሩክ ታደለ እና የግብ ጠባቂው ምንተስኖት ጊንቦን ውል ለማራዘም ተስማምተው ቃልኪዳን ዘላለም፣ ብሩክ በየነ ፣ ሙሴ ከቤላ ፣ ቃልአብ ውብሸት እና ሬድዋን ናስርን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ሐይቆቹ አሁን ደግሞ የግራ መስመር ተከላካዩ ደስታ ዮሐንስ ለማስፈረም ተስማምተዋል።

በዛሬው ዕለት ወደ አሳዳጊ ክለቡ ሀዋሳ ከተማ ለመመለስ የተስማማው ደስታ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በተጨማሪም በሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ችሏል።