የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ አጥቂ ወደ ታንዛኒያ አምርታለች።

በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እየተጫወተች የምትገኘው መሳይ ተመስገን ወደ ታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ አምርታለች።
መሻዋን ከወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አድርጋ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ መቻል እና ንግድ ባንክ ቆይታ የነበራት አጥቂዋ በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሁሉም እርከኖች መጫወት ስትችል በያንግ አፍሪካንስ መፈረሟ በይፋ ባይረጋገጥም ብዙ ስምምነቶች እንዳለቁ የሰማን ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።
በታንዛኒያ ያንግ አፍሪካንስ ኢትዮጵያዊቷ አረጋሽ ካልሳ እየተጫወተች የምትገኝ ሲሆን ሌላኛው የታንዛኒያ ክለብ ሲምባ ኩዊንስ ሴናፍ ዋቁማን ማስፈረሙ ይታወቃል።

