ፍፁም አለሙ አዳማ ከተማን ተቀላቀለ

ፍፁም አለሙ አዳማ ከተማን ተቀላቀለ

በመቐለ 70 አንደርታ ድንቅ ዓመት ያሳለፈው ፍፁም ዓለሙ ወደ አዳማ ከተማ አቀና

በደሴ ከተማ እግርኳስን የጀመረው ታታሪው አማካይ ፍፁም አለሙ በፋሲል ከነማ ፣ በባህር ዳር ከተማ፣ በመቻል እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከመቐለ 70 እንድርታ ጋር በግሉ የተሳካ ጊዜ ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን በክረምቱ የዝውውር መስኮትም ቀጣይ መዳረሻው የት ይሆናል የሚለው ብዙዎች ሲጠብቁት የነበረ ዜና ነው። ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ መሰረት ማረፊያው ክለብ አዳማ ከተማ ሊሆን መቃረቡን አውቀናል። ከደቂቃዎች በፊት በሁለቱ አካላት መካከል ከተካሄደው እና በስኬት ከተጠናቀቀው ድርድርም ተጫዋቹ ወደ አዳማ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።