የጣና ሞገዶቹ የሁለት ነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል አራዝመዋል

የጣና ሞገዶቹ የሁለት ነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል አራዝመዋል

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች የሁለት ተጫዋቾቻቸውን ውል ማራዘማወቸው ታውቋል።

በአሰልጣኝ ደገአረገ ይግዛው የሚመሩት ባህር ዳሮች የሽመልስ በቀለ ፣ ዩዳሄ ዳዊት፣ ኪቲካ ጅማ፣ አስራት ቱንጆ ለማፈረም ተስማምተው የወንደሰን በለጠን ውል ማራዘማቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ የወንድሜነህ ደረጄ እና የአንበሉን በረከት ጥጋቡን ውል ማራዘማቸው ታውቋል።

አብዛኛው የእግርኳስ ህይወቱን በባህርዳር ከተማ ያሳለፈው በረከት በወልቂጤ ከተማ፣ በአማራ ፖሊስ ሲጫወት የቆየ ሲሆን ያለፉትን አራት ዓመታት ቡድኑን በወጥነት ሲያገለግል ቆይቶ አሁን ደግሞ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት መስመማቱ ታውቋል። ሌላኛው ውል ያራዘመው ተከላካዩ ወንድሜነህ ደረጀ ሲሆን በልደታ ክፍለ ከተማ፣ በሱሉልታ በኢትዮጵያ ቡና ከተጫወተ በኋላ ባለፉት ሁለት ዓመታት በቆየበት ባህር ዳር ቆይታው ለማራዘም ለሁለት ዓመት ለመቆየት መስመማቱ አውቀናል።