ወልዋሎዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

ወልዋሎዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው አማካይ ወደ ቢጫዎቹ አመራ።

በዛሬው ዕለት በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያ ውድድር ተጋጣሚያቸው የሚያውቁት ወልዋሎዎች የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሰባተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል። ቡድኑን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ተጫዋች ደግሞ አቤል እንዳለ ነው።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው አማካዩ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የእግርኳስ ህይወቱን ጀምሮ በመቀጠል ደግሞ በደደቢት፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም በሲዳማ ቡናና ፋሲል ከነማ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ዳግሞ ወደ ወልዋሎ ለማቅናት ከስምምነት ደርሷል።