የሊጉ ኮከብ ግብ ጠባቂ ማረፍያው ታውቋል

የሊጉ ኮከብ ግብ ጠባቂ ማረፍያው ታውቋል

ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየው ሴኔጋላዊ ግብ ጠባቂ ማረፊያው የት እንደሆነ ታውቋል።

በሀገሩ ክለቦች ኒያሪ ፣ ጃራፍ እና ጄነሬሽን ፉት እንዲሁም በዴንማርኩ ጃመር ቡጌት ከተጫወተ በኋላ ላለፉት የውድድር ዓመታት በባህርዳር ከተማ ስኬታማ ቆይታ ያደረገው ሴኔጋላዊው የግብ ዘብ ፔፔ ሰይዶ የውል ዘመኑ መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣይ ማረፊያው በብዙዎች የሚጠበቅ ሆኗል። የተለያዩ ክለቦች የተጫዋቹ ፈላጊ ሆነው ቢቀርቡም ግብ ጠባቂው ለተጨማሪ ዓመት በባህር ዳር ከተማ ለመቆየት መስማማቱን አውቀናል።

የዴንማርኩን ክለብ ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ ወዲህ በኮከብ ግብ ጠባቂዎች ምርጫ ላይ ዕጩ ሆኖ ይቀርብ የነበረው ቁመተ መለሎው ግብ ጠባቂ የ2018 የሲቢኢ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኖ መሸለሙ ሲታወቅ በጣና ሞገዶቹ ቤት ለመቆየት መስማማቱ ለክለቡ አስደሳች ዜና ነው።