መቻል ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉን አስፈረሙ

በአሰልጣኝ ውበቱ የሚመሩትና ቀደም ብለው የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ራሰቸውን ያጠናከሩት መቻሎች አሁን ደግሞ ግብ ጠባቂእ መክብብ ደገፉን የግላቸው አድርገዋል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በመቐለ 70 እንደርታ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ መጫወቱ ይታወሳል።

