ወጣቱ የግብ ዘብ ዐፄዎቹን ተቀላቅሏል

ወጣቱ የግብ ዘብ ዐፄዎቹን ተቀላቅሏል

ፋሲል ከነማዎች ወጣቱን የግብ ዘብ ማስፈረማቸው እርግጥ ሆኗል።

በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የሚመሩት ፋሲል ከነማዎች ዘግይተውም ቢሆን ወደ ዝውውሩ በመግባት የፍሬዘር ካሳን ፣ ዮሴፍ ዮሐንስን እና አሚር ሙደሲርን ዝውውር ማጠናቃቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ ወጣቱን ግብ ጠባቂ አብዩ ካሳሁንን ማስፈረማቸው እርግጥ ሆኗል።

የእግርኳስ ሕይወቱን በድሬደዋ ታዳጊ ቡድን የጀመረው አብዩ ያለፉትን ዓመታት በድሬዳዋ ከተማ በዋና ቡድን ሲያገለግል ቆይቶ አሁን ሁለተኛ ክለቡ ሊሆን ለዐፄዎቹ ለሁለት ዓመት ፈርሟል።