የጣና ሞገዶቹ አማካይ አስፈረሙ

የጣና ሞገዶቹ አማካይ አስፈረሙ

በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ወጣቱ አማካይ ወደ ባህርዳር ከተማ አቀና

አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረምና የነባሮቹን ውል በማራዘም ቡድናቸውን በማጠናከር ላይ የሚገኙት ባህርዳር ከተማዎች ባለፉት ሦስት ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ወጣቱ አማካይ ኬኔዲ ገብረፃድቕን አስፈረሙ። በተጠናቀቀው ዓመት በአመዛዡ ቋሚ ተሰላፊ ሆኖ ዓመቱን ያጠናቀቀው አማካዩ ከዚህ ቀደም ለጥቂት ወራት በደደቢት ቆይታ ማድረጉ ሲታወስ አሁን ደግሞ ከሦስት ዓመታት የመቐለ ቆይታ ወደ ባህርዳር ከተማ አቅንቷል።