በአንደኛ ሊግ በሆምሻ ሸንጋ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው የመስመር አጥቂ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ክለብ አመራ

በአንደኛ ሊግ ሲሳተፍ በነበረው እና የውድደሩ አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን ወደ ከፍተኛ ሊግ ማደግ በቻለው በሆምሻ ሸንጋ ስብስብ ውስጥ የነበረው የመስመር አጥቂ መሐመድ አብዱላዚዝ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመጫወት መስመማቱን አውቀናል። ተስፈኛው የግራ መስመር አጥቂው መሐመድ አብዱላዚዝ ቡድኑ ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲያድግ ጎሎችን በማስቆጠር ትልቅ አበርክቶ የነበረው ተጫዋች ሲሆን አሁን ደግሞ በሀምራዊ ለባሾቹ ለሁለት ዓመት ለመጫወት ተስማምቷል።

