የአዲስ ግደይ ቀጣይ ማረፊያ የት ይሆን?

የአዲስ ግደይ ቀጣይ ማረፊያ የት ይሆን?

የሀምራዊ ለባሾቹ አምበል አዲስ ግደይ ቀጣይ የማረፊያው የት ይሆን?

ከአጋሮ የተገኘው አዲስ ግደይ በሲዳማ ቡና ረጅም ዓመት ቆይታ በማድረግ ወደ ፈረሰኞቹ ቤት በመምጣት በዋንጫ የታጀበ ቆይታ ካደረገ በኋላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ሀምራዊ ለባሾቹ ቤት ቆይታ ሲያደርግ በ2016 የሊጉን ቻምፒዮንነት ክብር አሳክቷል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አስራ አንድ ጎሎችን በማስቆጠር የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ አራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አዲስ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር እየተያያዘ ይገኛል።

ይህን ተከትሎ ሶከር ኢትዮጵያ ባደረገችው ማጣራር ምንም እንኳን ተጫዋቹ የውል ዘመኑ ጥቅምት 30 ቀን 2019 የሚጠናቀቅ ቢሆነም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስን አስቀርተው ውሉን ለማራዘም ሁለት የድርድር ቀናቶችን ያሳለፉ ቢሆንም እስካሁን ዝውውርሩን ማጠናቀቅ አልቻሉም። በሌላ በኩል ፋሲል ከነማ ሌላኛው የተጫዋቹ ፈላጊ ክለብ ሆኖ ብቅ ያለ ሲሆን ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንዳለ እና ለዐፄዎቹ የመፈረም ዕድሉ ሰፊ እንደሆነ ሰምተናል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።