ብሩክ ሰሙ በባህር ዳር ከተማ ቤት የሚያቆየውን ውል አራዘመ።

የጣና ሞገዶቹ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የቡድን ስብስባቸውን የማጠናከር እና የማደስ ስራቸውን ቀጥለዋል። ከዚህ ቀደም በመቻል፣ ወልዋሎ፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ሸገር ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ቤንች ማጂ ቡና ተጫውቶ ያሳለፈው ብሩክ ሰሙ በባህር ዳር ከተማ ቤት የሚያቆየውን አዲስ ውል በይፋ አራዝሟል።
በአማካይ እንዲሁም በመስመር አጥቂነት ቦታዎች ላይ መሰለፍ የሚችለው ይህ ሁለገብ ተጫዋች፣ በጣና ሞገዶቹ ቤት ባሳለፈው ቆይታ አመርቂ ብቃት ማሳየት የቻለ ሲሆን አሁንም በውሃ ሰማያዊው ማሊያ ለመቀጠል የሚያስችለውን አዲስ ውል በመፈረም በባህር ዳር ከተማ ቤት መቆየቱ ተረጋግጧል።

