አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ተያይዘውታል
ከዚህ ቀደም ኮንኮኒ ሀፍዝ ፣ ካሌብ አማንክዋህ እና ሳምባ ሴክ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰው የነባር ተጫዋቾችን ውል ያራዘሙት አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች አሁን ደግሞ የመስመር አጥቂው ፍስሀ ቶማስ የግላቸው አድርገዋል። ከዚህ ቀደም በአዳማ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ ፣ አረካ ከተማ ፣ እንጅባራ ከተማ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን ቆይታ ያደረገው የፊት መስመር ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ወደ በርበሬዎቹ አቅንቷል።

