ከአርባምንጭ ጋር ቆይታ የነበራቸው ሁለቱ ተጫዋቾች ማረፊያቸው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሆኗል።

በስፋት ወደ ዝውውሩ በመግባት ፍራኦል መንግስቱ ፣ አንዋር ሙራድ እንዲሁም በከፍተኛ ሊጉ አማኑኤል ግዛቸው እና እሱባለው ሙሉጌታ ለማስፈረም ተስማምተው የአቤል ሀብታሙን እና የሌሎች ነባር ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ከስምምነት የደረሱት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አሁን ደግሞ የመስመር ተጫዋቹ አሸናፊ ተገኝ እና የተከላካይ አማካዩ እንዳልካቸው መስፍንን አስፈርመዋል። ሁለቱም ተጫዋቾች በአርባምንጭ እና በጋሞ ጨንቻ ተጫውተው ያሳለፉ ሲሆን አሁን ደግሞ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ለመፈረም ተስማምተዋል።

