በተጠናቀቀው ዓመት በባህርዳር ከተማ ቆይታ የነበረው አማካይ ወደ ቢጫዎቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል

በትናንትናው ዕለት ሴኔጋላዊው ግብ ጠባቂ አማር ፋል ለማስፈረም ተስማምተው የግብ ጠባቂው ናትናኤል ኪዳነ እና የቀኝ መስመር ተከላካዩ ናሆም ሃይለማርያምን ውል ያራዘሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በባህርዳር ከተማ ቆይታ የነበረው ጋናዊው ሰቲህ ኦሴን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
ኢለቨን ወንደርስ ከተባለ የሀገሩ ክለብ እግር ኳስን የጀመረው በአማካይነት እና በመስመር ተጫዋችነት መሰለፍ የሚችለው ይህ ጋናዊ ባለፉት ዓመታት በሀገሩ ክለቦች አሻንቲ ጎልድ እና አሻንቲ ኮቶኮ እንዲሁም በግብፁ ክለብ ባላዲያት እና በእስራኤሉ ሃፖል ክፋር ሳባ መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአንድ ዓመት የባህርዳር ከተማ ቆይታ ወደ ወልዋሎ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

