በሴካፋ ዞን የቻምፒየንስ ሊግ የማጣሪያ ውድድር ሀገራችንን ለስድስተኛ ጊዜ የሚወክለው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገ ለሊት ወደ ሩዋንዳ ያመራል።

በሴቶች እግርኳስ ስኬታማ በሆነው አሠልጣኝ ብርሀኑ ግዛው የሚመራውና በሀገር ውስጥ ውድድሮች ዘጠኝ ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በማንሳት የሚስተካከለው ቡድን የሌለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘንድሮም በአህጉራዊ ውድድር ለመሳተፍ የቀጠናውን የማጣሪያ ፍልሚያ ሩዋንዳ ላይ የሚያከናውን ሲሆን ቡድኑም ያለፉትን ሳምንታት መቀመጫውን አዳማ ከተማ ላይ በማድረግ ዝግጅቱን ሲያከናውን ቆይቷል።
ለተከታታይ 6ጊዜ ሊጉን በማሸነፍ አዲስ ታሪክ የሰራው ቡድኑ ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ ለተከታታይ 11 ቀናት በሩዋንዳ ርዕሰ መዲና ኪጋሊ ጨዋታዎቹን የሚያደርግ ሲሆን በነገው ዕለት ለሊትም ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ታውቋል። ቡድኑም ወደ ስፍራው 20 ተጫዋቾችን፣ 7 የአሠልጣኝ ቡድን አባላትን እና 3 የአስተዳደር ኃላፊዎችን አጠቃላይ 30 የልዑካን ቡድን ይዞ እንደሚጓዝ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ወደ ስፍራው የሚያቀኑ የልዑካን ቡድን አባላትም እንደሚከተለው ተቀምጧል።
ተጫዋቾች
1)ታሪኳ በርገና
2)አበባ አጀቦ
3)ቅድስት ዘለቀ
4)ትእግስት አዳነ
5)ሀሳቤ ሙሶ
6)ብዙአየሁ ታደሰ
7)በሻዱ ረጋሳ
8)ናርዶስ ጌትነት
9)ታሪኳ ደቢሶ
10)አለምነሽ ገረመው
11)ኝቦኝ የን
12)ምህረት አየለ
13)እጸገነት ግርማ
14)ሰናይት ቦጋለ
15)የምስራች ላቀው
16)እሙሽ ዳንኤል
17)ማህሌት ምትኩ
18)ሊዲያ እያሱ
19)ረድኤት አስረሳኸኝ
20)ምርቃት ፈለቀ
የአሠልጣኞች ቡድን አባላት
1) ብርሃኑ ግዛው ( ዋና አሰልጣኝ)
2)ሽመልስ ጥላሁን (ምክትል አሰልጣኝ)
3)አብዱልከሪም ሀሰን (የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ)
4)ተሾመ መተኪያ (ቡድን መሪ)
5)ስንታየው ተሾመ (ፊዚዮቴራፒ)
6) ዶ/ር ቃልኪዳን ዘገየ (የህክምና ባለሙያ)
7)መሀመድ ከድር (ትጥቅ ያዥ)

