የቴራንጋ አናብስት አዲስ አሰልጣኝ ሾመዋል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ በተደለደሉበት ምድብ የምትገኘው እና በመስከረም አጋማሽ በባህርዳር ስታድየም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋር የምትጫወተው ሴኔጋል የቀድሞ የአርሰናል አምበል ፈረንሳዊው ፓትሪክ ቪዬራ መሾሟን ይፋ አደረገች።
በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የተወለደው እና ፈረንሳይን በዓለም አቀፍ መድረክ ወክሎ የ1998 የዓለም ዋንጫ እና የ2000 የአውሮፓ ዋንጫ ያነሳው አማካዩ በክለብ እግር ኳስ ቆይታው ሦስት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫዎች ያነሳበትን አርሰናል ጨምሮ በኤሲሚላን ዩቬንቱስ፣ ኢንተር ሚላን እና ማንቸስተር ሲቲ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን ወደ አሰልጣኝነት ሙያ ከገባ በኋላ ደግሞ በኒውዮርክ ሲቲ፣ ኒስ፣ ክሪስታል ፓላስ፣ ስትራስበርግ እና ጄኖዋ ማሰልጠኑ ይታወቃል።
የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ አሁን ደግሞ የትውልድ ሀገሩን ለማሰልጠን ከስምምነት የደረሰ ሲሆን በቅርቡ በይፋዊ ስነ ስርዓት ፌርማውን እንደሚያኖር የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።

