በሞሮኮ በተሰናዳው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ከሊጋችን በብቸኝነት መሳተፍ የቻለው የግብ ዘቡ አልዮንዜ ናፍያን ማረፊያው ታውቋል።

ወደ ሀገራችን ከመጣ ወዲህ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከመቻል ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ዩጋንዳዊ ግብ ጠባቂ አልዮንዜ ናፍያን ከመቻል ጋር የውል ዘመኑ መጠናቀቁን ተከትሎ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ክለቦች ሲፈለግ ቢቆይም በስተመጨረሻም ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ለመጫወት መወሰኑን አውቀናል።
ከዚህ ቀደም ለስድስት ዓመታት ካገለገለበት የሀገሩ ዩ አር ኤ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራችን የመጣው ግብ ጠባቂው ያለፉትን ሁለት ዓመታት በመቻል ያሳለፈ ሲሆን ከ2022 ጀምሮ ሳያቋርጥ ለሃገሩ ዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለ መሆኑ ሲታወቅ አሁን ኢትዮ ኤሌክትሪክን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

