አቶ ኢሳይያስ ጂራ መግለጫ ሊሰጡ ነው

አቶ ኢሳይያስ ጂራ መግለጫ ሊሰጡ ነው

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ነገ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጡ ነው።

ከሰሞኑ በስፖርት ቤተሰቡ መነጋገሪያ ከነበሩ ጉዳዮች ቀዳሚ የነበረው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፉት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በብቸኝነት እጩ ሆነው መቅረባቸው ነበር።

ይህን ተከትሎ በዚህ ጉዳይ ላይ ከስፖርት ቤተሰቡ አሉታዊም ሆነ አውንታዊም ምላሽ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ላይ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው በብቸኝነት የቀረቡት አቶ ኢሳይያስ በዚሁ ጉዳይ እና የእሳቸው የካቢኔ አባላት ስላሰቧቸው ተግባራት እንዲሁም በሚነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት ነገ ወሎ ሰፈር በሚገኘው ቤስት ዌስተርን ሆቴል ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ የጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ ለሚዲያዎች ማድረጋቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።