ከዋልያዎቹ ስብስብ ተጫዋቾች መቀነሳቸውን ቀጥለው የመቻሉ ተከላካይም ከስብስቡ ውጭ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዚህ ወር ከሱዳን እና ከሴኔጋል ለሚጠብቁት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች አስቀድመን ባደረስናቹሁ መረጃ መሰረት አጥቂው ታምራት እያሱ እና የመስመር ተጫዋቹ ፀጋአብ ግዛው መቀነሳቸውን ዘግበንላቹሁ ነበር (በትናንትናው ዕለት ደግፌ ዓለሙ መቀነሱ ልብ ይሏል)።

አሁን ደግሞ ያለፉት አራት ሳምንታት ከቡድኑ ጋር ሲዘጋጅ የቆየው እና ዘንድሮ መቻልን የተቀላቀለው ተከላካዩ አማኑኤል ተርፉም ከስብስቡ መቀነሱን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

