በአሁኑ ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሜዳ ልምምዱን እየሰራ ባለው የብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውስጥ ሁለት ተጫዋቾች አለመገኘታቸውን አይተናል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ መስከረም 13 ቀን ከሱዳን እንዲሁም መስከረም 19 ቀን ከሴኔጋል ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን ማድረግ ቀጥሏል። ቡድኑ ዛሬ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሜዳ እያደረገ ባለው ልምምድ ላይም ሁለት ተጫዋቾች አለመገኘታቸው ሶከር ኢትዮጵያ በቦታው ተገኝታ ለማረጋገጥ ችላለች።
ሁለቱ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ እና ተከላካዩ ሮሆቦት ስላሎ ሲሆኑ በዛሬው ልምምድ ያለ መገኘታቸው ምክንያት የፓስፖርት ጉዳይ ለመጨረስ እንደሆነ ያጣራን ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ተመልሰው ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

