ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋል

በ2027 በጎረቤት ሀገራት ታንዛንያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎችን ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኘው እና በመስከረም ወር አጋማሽ ከሱዳን እና ከሴኔጋል አቻዎቹ ጋር የሚጫወተው በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቀናት በኋላ በእለተ ሰምበት በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ከሚመራው ሀዋሳ ከተማ ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋል።
ዝግጅት ከጀመረ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ከኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ሦስተኛው የአቋም መለክያ ጨዋታውን እሁድ ረፋድ 03:00 ሰዓት በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ስታዲየም ያደርጋል።

