በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ ከሱዳን ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ የሚመሩ አልቢትሮች ታውቀዋል።

በአሠልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዘለግ ላለ ጊዜ ሲዘጋጅ ቆይቶ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ወደሚያደርግበት ደቡብ ሱዳን አምርቷል። በቀናት ልዩነት ሱዳን እና ሴኔጋልን የሚገጥመው ቡድኑ ጁባ ላይ የሚጠብቀውን ፍልሚያ ላይቤሪያዊያን ዳኞች እንደሚመሩት ታውቋል።
ዓርብ ምሽት 1 ሰዓት የሚደረገውን ጨዋታ ዋሽንግተን ኤን ዶሎ ከረዳቶቻቸው ጆኤል ዎንካ ዎንካ ዶይ እና ቶማስ ኤን ኮኔህ እንዲሁም አራተኛ ዳኛው ሞሰስ ቢ ጆንሰን ጋር እንደሚመሩት ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

