አምስት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ሀገራቸውን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ይሳተፋሉ

በኬኒያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ለመጫወት ለሀገራችን ቡድኖች ፊርማቸውን ያኖሩ አምስት የውጪ ሀገር ተጫዋቾችም ለሀገራቸው የማጣሪያ ጨዋታዎች መመረጣቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።
በዚህም መሠረት
* የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ የተከላካይ አማካዩ ሰይዱ ባህ ካማራ እና የወላይታ ድቻው አማካይ ሳይዱ ፎፋናህ ለሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን
* የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ሴርጌ ኦባሳ ለቤኒን ብሔራዊ ቡድን
* የመቻሉ ግብ ጠባቂ መሐመድ ካማራ ለጊኒ ብሔራዊ ቡድን
* የኢትዮጵያ ቡናው አማካይ ታይባ ምቦኙምዋሚ ለሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን
በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያው ላይ የሚሳተፉ ይሆናሉ።

