“አሁን ከሜዳችን ውጪ ብንጫወትም ጥሩ ውጤት ይዘን እንሄዳለን ብዬ አስባለው” ያሬድ ባዬ

ነገ ምሽት 1 ሰዓት ኢትዮጵያ እና ሱዳን ከሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ አስቀድሞ የዋልያዎቹ አለቃ ዩሐንስ ሳህሌ እና አምበሉ ያሬድ ባየ ከደቂቃዎች በፊት የቅድመ ጨዋታ አስተያየት ጁባ ላይ ሰጥተዋል። የቡድኑ አምበል ያሬድ ቡድኑ ከሜዳው ውጪ መጫወቱ ስለሚፈጥርባቸው ጫና እንዲሁም ስለዝግጅት ጊዜያቸው እና ድጋፍ ተጠይቆ የሰጠውን ምላሽ እንደሚከተለው ቀርቧል።
ያሬድ ሀሳቡን በስፍራው ለተገኙ የነገናኛ ብዙሀን ሲሰጥ “ብዙ ጨዋታዎችን ከዚህ በፊት ከሜዳችን ውጩ ነው የተጫወትነው ፤ ሜዳችን ላይ ብዙ አልተጫወትንም። ከሜዳችን ውጪ ወጥቶ መጫወትን ለምደነዋል። ደጋፊያችንን ደግሞ ከሴኔጋል ጋር በምናደርገው ጨዋታ የምናገኘው ይሆናል። አሁን ከሜዳችን ውጪ ብንጫወትም ጥሩ ውጤት ይዘን እንሄዳለን ብዬ አስባለው።”
አምበሉ ሀሳቡን ቀጥሎ “ረጅም ጊዜ ተዘጋጅተናል። ደቡብ ሱዳን ሌላኛው ቤታችን ነው ብዬ ነው የማስበው። ብዙ ኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲ ስላለ መጥተው ይደግፉናል ብዬ አስባለው።” በማለት ተናግሯል።

