ኮከቧ በባንክ ቤት ለቆየት ተስማምታለች

ኮከቧ በባንክ ቤት ለቆየት ተስማምታለች

በአብዩ አረጋሽ

የ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕርሚየር ሊግ ኮከብ ተጨዋቿ ከክለቧ ጋር ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ውሏን አድሳለች።

የመጀመሪያ የእግርኳስ ክለቧን በአርባምንጭ የጀመረችው  እመቤት አዲሱ ከአርባምንጭ በመቀጠል ለመቻል እንዲሁም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጫወቷ አይዘነጋም። በተለይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በ 7 አመት ቆይታ 6 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እና 1 ኢትዮጵያ ላይ የተዘጋጀውን የምስራቅ አፍሪካን ዋንጫ ማሳካት ችላለች። ተጫዋቿ በግሏ በ2017 ዓ.ም የአመቱ ምርጥ ተጨዋች እጩ የነበረች ሲሆን በ2018 ዓ.ም የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ክብርንም ማግኘቷ ይታወቃል።

እመቤት በዘንድሮው ሩዋንዳ ኪጋሊ ላይ በተዘጋጀው የምስራቅ አፍሪካ ውድድር በጉዳት ምክንያት ያልተሳተፈች ሲሆን አሁን  ላይ በሙሉ ጤንነት ላይ በመገኘት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ለተጨማሪ 2 አመት የሚያቆያትን ውል በዛሬው ዕለት ተፈራርማለች።